Welcome to
Home የቴክኒክና ሙያ ሴት አሰልጣኞችና አመራሮች ፎረም በአዲስ አበባ ተመሰረተ።

የቴክኒክና ሙያ ሴት አሰልጣኞችና አመራሮች ፎረም በአዲስ አበባ ተመሰረተ።

23rd January, 2026

የቴክኒክና ሙያ ሴት አሰልጣኞችና አመራሮች ፎረም በአዲስ አበባ ተመሰረተ።

ጥር 13/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሴት አሰልጣኞችና አመራሮች ፎረም በዛሬው ዕለት በይፋ ተመስርቷል።

ፎረሙ ለሴት ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና አመራሮች ምቹ እና ደጋፊ የስልጠና እንዲሁም የስራ አካባቢ በመፍጠር፣ ወቅቱ የሚጠይቀውን ክህሎት እንዲጨብጡ በማገዝ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ እንደሚያስችል ተገልጿል።

በፎረሙ የምስረታ መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ ባደረጉት ንግግር፣ የፎረሙ መመሰረት የማህበረሰቡ ግማሽ አካል የሆኑ ሴቶችን ወደፊት በማምጣት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

እንዲሁም ፎረሙ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ውስጥ ብቃትን ማዕከል ያደረገ ተወዳዳሪና ነባራዊ ሁኔታዎችን የሚገነዘቡ ጠንካራ ሴት አመራሮችን ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል ለሴቶች አዳጋች ናቸው ተብለው የሚታወቁ የስልጠና ዘርፎችን ሴቶች እንዲቀላቀሉ በማበረታታት፣ በየደረጃው የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ፎረሙ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተጠቁሟል።

በምስረታ መርሀ ግብሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ የትምህርትና ስልጠና፣ የሀብት ማፈላለግ እና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችን ጨምሮ የተለያዩ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተካሂዷል።

.

Copyright © All rights reserved.