Welcome to
College አራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የዘርፉ እሳቤ በሚገባ ስለ መተግበሩ ማሳያ መሆኑ ተገለፀ።

አራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የዘርፉ እሳቤ በሚገባ ስለ መተግበሩ ማሳያ መሆኑ ተገለፀ።

09th May, 2025

አራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የዘርፉ እሳቤ በሚገባ ስለ መተግበሩ ማሳያ መሆኑ ተገለፀ።
ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው አራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በውድድሩ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮን ጨምሮ በሀገሪቱ የሚገኙ ብሄራዊ ክልል የዘርፉ መዋቅሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ የዝግጅት ክፍላችን ቅኝት ባደረገበት ወቅት ለመረዳት ችሏል።
እንደ አዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሰልጣኝ ዘርፍ በ19 የሙያ አይነቶች በክህሎት ውድድር፤አንድ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እንዲሁም በአሰልጣኝ አስር፣ በሰልጣኝ አንድ እና በኢንተርፕራይዝ አንድ በድምሩ 13 ቴክኒዎሎጂዎች በ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ መቅረባቸውን በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኖሎጂ ምርምር ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ቶልቻ ተናግረዋል።
የክህሎት ውድድሩ የዘርፉ እሳቤ በሚገባ ስለ መተግበሩ ማሳያ ከመሆኑም በላይ የአሰልጣኞች እና ሰልጣኞችን አቅም በመፈተሽ ቴክኖሎጂ መቶ በመቶ የመቅዳት አቅም የደረሰበትን ደረጃ ለመገንዘብ እንደሚያስችል አቶ ሲሳይ ጨምረው ገልፀዋል።
በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሚያዚያ 27 ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የክህሎት ውድድር እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም የሚዘልቅ ይሆናል።
.

Copyright © All rights reserved.