Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በአዲሰ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሪፎርምና መደበኛ ስራዎች አፈፃፀም በከፍተኛ አመራር የተካሄደ ሱፐርቪዥን የግብረ-መልስ መድረክ ተካሄደ።
በአዲሰ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሪፎርምና መደበኛ ስራዎች አፈፃፀም በከፍተኛ አመራር የተካሄደ ሱፐርቪዥን የግብረ-መልስ መድረክ ተካሄደ።
17th May, 2025
በአዲሰ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሪፎርምና መደበኛ ስራዎች አፈፃፀም በከፍተኛ አመራር የተካሄደ ሱፐርቪዥን የግብረ-መልስ መድረክ ተካሄደ።
ግንቦት 5/2016 ዓ ም
የኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚንስቴር በከተማ አስተዳደሩ ለአንድ ወር ሲያካሂድ የቆየውን የድጋፍ እና ክትትል ስራ በማጠናቀቅ የከተማው ከፍተኛ የፓርቲ እና የመንግስት አመራሮች በተገኙበት አቅርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
የክትትልና ድጋፍ ግብረ-መልሱን ያቀረቡት የስራና ክህሎት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራውን በንቅናቄ የመራበትን አግባብ እና ፀጋዎችን በአግባቡ ከመለየት አንፃር የተሠሩ ስራዎችን አድንቀው እነዚህ ተግባራት በቀጣይም ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በመድረኩ በሰጡት አስተያየት ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በከተማ አስተዳደሩ በነበረው የአንድ ወር ቆይታ ችግሮችን መለየት ብቻ ሳይሆን መፍትሄ እየሰጠ እና የአመራሩን እና የፈፃሚውን አቅም በስልጠናዎች ሲገነባ እንዳሳለፈ ገልፀው ይህም ለቢሮው ትልቅ አቅም ፈጥሮለታል ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ የሥራና ክህሎት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ለፍቶ ደክሞ ሃብት ማፍራት የሚችል እና በአመለካከት የተለወጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር መልፋት እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ ሞገስ አያይዘውም የዘርፉ ተልዕኮ በአንድ ቢሮ ብቻ ተጀምሮ የሚያልቅ አለመሆኑን ገልፀው ሁሉም የሚመለከተው ሴክተር ለጉዳዩ ፖለቲካዊ ትርጉም ሰጥቶ ሃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አለማየሁ እጅጉ፣ የቢሮው የዘርፍ ኃላፊዎችና አማካሪዎች እንዲሁም የሥራና ክህሎት ሚንስቴር አመራሮች ተገኝተዋል።
.