Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዋቀረ ድጋፍና ክትትል ቡድን የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ ጀመረ።
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዋቀረ ድጋፍና ክትትል ቡድን የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ ጀመረ።
17th May, 2025
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዋቀረ ድጋፍና ክትትል ቡድን የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ ጀመረ።
ግንቦት 5/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዋቀረ ድጋፍና ክትትል ቡድን በ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወር ምዘና ግብረ መልስ መነሻ በማድረግ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ ጀምሯል።
የድጋፍና ክትትሉ ዋና ዓላማ በበጀት ዓመቱ የስድስት ወራት ምዘና በተሰጠ ግብረ መልስ መነሻነት በቢሮውና በዘርፉ መዋቅሮች የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በመፈተሽ ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚያስችል የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዳይዜሽን ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ በቀለ ተናግረዋል።
ድጋፍና ክትትል ቡድኑ በቢሮው የሚገኙ 21 ዳይሬክቶሬቶችን ጨምሮ ለቢሮው ተጠሪ የሆኑ በ11ዱ ክፍላተ ከተሞች ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት እና በ15ቱ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ድጋፍና ክትትል እንደሚያካሂድ ዳይሬክተሯ ጨምረው ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለትም የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት እና በወረዳ ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በስምንት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ አተኩሮ ድጋፍና ክትትል እንደሚካሄድ እና በሰነድ ፍተሻ እና በምልከታ ተግባራቱ የተከናወኑበትን ሁኔታ በመቃኘት መልካም ተሞክሮዎች እንዲሰፉና ደካማ አፈፃፀሞች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያስችላል ተብሏል።
.