Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የፅድቀት ምጣኔያቸውን ለመጨመር በቋሚነት መንከባከብ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የፅድቀት ምጣኔያቸውን ለመጨመር በቋሚነት መንከባከብ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
21st May, 2025
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የፅድቀት ምጣኔያቸውን ለመጨመር በቋሚነት መንከባከብ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
ግንቦት 9/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በስድስተኛው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የተተከሉ ችግኞች እንክካቤ መርሀ ግብር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አካሂዷል።
የእንክብካቤ መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ ቢሮው በስድስተኛው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ከ120ሺ በላይ ችግኞችን መትከሉን በማስታወስ የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች በቋሚነት እንዲንከባከቡ በመደረጉ የችግኞች የመጽደቅ ምጣኔን ለመጨመር አስችሏል ብለዋል።
አቶ አስፋው አክለውም መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተከትሎ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን የሚደርስባቸውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ 154ሺ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይፋ ባደረገው ፕሮጀክት ተጠቃሚዎቹ በአካባቢ ልማት ስራ ላይ እንዲሰማሩበመደረጉ የአካባቢ ስነ ምህዳርና የአየር ንብረት ሁኔታ በማስተካከል ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ገልፀዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒመተላ ከበደ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ችግኞችን በዘመቻ ከመትከል ባለፈ እንዲፀድቁ መንከባከብ ያልተለመደ ተግባር በመሆኑ ቢሮው በዘመቻ የተተከሉ ችግኞችን በቋሚነት በመንከባከቡ ከ87 በመቶ በላይ መፅደቅ መቻላቸውን ጠቁመዋል።
በችግኝ እንክብካቤ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ እና የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ተገኝተዋል
.