Welcome to
College የክፍለ ከተማው አስተዳደር የስራ እድል ፈጠራ የሌማት ቱሩፋት ስራዎችና የተግባራቶቹ ኦዲት ሪፖርት ላይ በመወያየት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

የክፍለ ከተማው አስተዳደር የስራ እድል ፈጠራ የሌማት ቱሩፋት ስራዎችና የተግባራቶቹ ኦዲት ሪፖርት ላይ በመወያየት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

09th May, 2025

የክፍለ ከተማው አስተዳደር የስራ እድል ፈጠራ የሌማት ቱሩፋት ስራዎችና የተግባራቶቹ ኦዲት ሪፖርት ላይ በመወያየት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማው አስተዳደር መደበኛና በንቅናቄ የተሰሩ የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራዎች አፈፃፀም እንዲሁም በወረዳዎች ሲካሄድ የቆየው የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ቱሩፋት የኦዲት ሪፖርት የክፍለ ከተማ አጠቃላይ አመራር እና የሁሉም ወረዳዎች የግብረ ሃይሉ አባላት በተገኙበት በዛሬው እለት ተወያይቷል ፡፡
በውይይቱ የክፍለ ከተማው የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ልሳነ ወርቅ ጣሰው በንቅናቄ የተከናወኑ የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን የክፍለ ከተማው ታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊና የኦዲት ቡድኑ ተወካይ አቶ አብዱራህማን ክብረት ደግሞ የሌማት ቱሩፋት እና የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች የኦዲት ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሒዶበታል።
ከስራ እድል ፈጠራ አንፃር ስራ አጦችን ልየታና ምዝገባ፣ስልጠና የማስገባት ስራ፣የሰራ እድል ፈጠራን ማጠናከር፣ ኢንተርፕራይዞች የመደገፍ፣ የብድር መስጠትና የማስመለስ ስራዎችን ማጠናከር ፤ በሌማት ቱሩፋት ተግባራትም ነባር ማስቀጠልና አዲስ ወደ ስራ ማስገባት ያሉበትን ደረጃ ተገምግሟል ።
ከኦዲት ሪፖርት ጋር ተያይዞም ከስራ አጥ ምዝገባ እስከ ስራ እድል ፈጠራና የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ማመቻቸት ድረስ ያሉት ሂደቶች በጥንካሬና በጉድለት የመለየት ስራን ጨምሮ በሂደቱ የተገኙ ተሞክሮዎች እና የተወሰዱ ልምዶች በሚያሳይ መልኩ ቀርቦ በዝርዝር ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበታል።
አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ የክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ እንደገለፁት የስራ እድል ፈጠራ እና የሌማት ትሩፋት ስራዎች አዳጊ ውጤቶችና ተሞክሮ የሚሆኑ ስራዎች መገኘታቸውን ገልፀው በተለይ በኦዲት ግኝቱ የተስተዋሉ ጉድለቶች በተሻለ ቅንጅት ወደ እቅድ ቀይሮ በመስራት በውጤት ማጠናቀቅ ይገባል ሲሉ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ።
የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሒም መሀመድ በበኩላቸው እስካሁን ያገኘናቸውን ውጤቶች በማስቀጠል በተለይ የመረጃ ጥራት ችግር ፣ ፀጋዎችን ያለመጠቀም እና ሌሎች ክፍተት የታየባቸው ዘርፎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት ጉድለቶችን በማስተካከል ለቀጣይ ስራችን በግብአትነት መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
.

Copyright © All rights reserved.